ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም ያላት ግዙፍ የኤሌክትሪክ ዕቃ ጫኝ መርከብ፣ የመጀመርያ የንግድ ጉዞዋን መጀመሯን ታዉቋል።
ይህን ተከትሎ ቻይና የኮንቴይነር ማጓጓዣ መርከቦቿን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል አማራጭ በመቀየር አዲስ የአረንጓዴ ምዕራፍ እንቅስቃሴ መጀመሯ ተዘግቧል።
በሻንጋይ የንግድ መርከቦች ዲዛይን እና ጥናት ተቋም ሙሉ አቅም የተሠራችው ይህች መርከብ፣ ሙሉ ለሙሉ በኤሌክትሪክ የምትሠራና ከካርቦን ልቀት ነጻ የሆነች የረቀቀ የቴክኖሎጂ ሥርዓት የተገጠመላት መሆኗ ተገልጿል።
መርከቧ 127.8 ሜትር ርዝመትና 21.6 ሜትር ስፋት ያላት ሲሆን፤ በጥቅሉ 20 ሺህ ኪሎ ዋት ሃውር (kWh) አቅም ያላቸው 10 ትላልቅ ባትሪዎች ተገጥመውላታል።
ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት ምንም ዓይነት የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀት የሌለው ከመሆኑም በላይ፣ መርከቧ በእንቅስቃሴ ወቅት ምንም ዓይነት ድምፅ እንደማታወጣ ተነግሯል።@SECO


