የወርቅ ዋጋ በአገር ውስጥ ገበያ ቀነሰ

-ዘርፉ ሳቢነቱ ቀንሷል እየተባለ ነው

በኢቢቪ

በባህረሰላጤው ጦርነት ሳቢያ የአገር ውሰጥ የወርቅ ዋጋ እስከ 16 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ተገለፀ።

በኢትዮጵያ በመካከለኛ እና ባህላዊ ደረጃ  የሚመረተው የወርቅ መጠን እና ማምረቻ ቦታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

በዚህም በተለይ ከኢኮኖሚ እና የምንዛሬ አሰራል ለውጡ ጋር በተያያዘ ወደ ብቸኛው የወርቅ ገዥ ወደ ሆነው ብሄራዊ ባንክ የሚመጣው መጠን በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው።

ሆኖም አሁንም በኮንትሮባንድ የሚወጣው ቀላል የማይባል መሆኑን ነው ዘርፉን የሚከታተሉ ለኢቢቪ የነገሩት።

 ምንም እንኳ ብሄራዊ ባንክ የተሻለ ቢከፍልም በተለያየ ምክንያት ህገወጥ መስመሩን የሚመርጡ አሉ የሚሉት የዘርፉ ባለመያዎች።

እንዲያም ሆኖ ባለሞያዎች ገለፃ የውዱ ብረት በአለም ገበያ ከሚታየው እውነታ በተቃራኒ በአገር ውስጥ ተረካቢዎች ፍላጎቱ ዋጋውም እየቀነሰ ነው።

አሁን እንደሚሰማው የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ  26 ሺ ብር አካባቢ ሲሆን። ይህ መጠን ከወራት በፊት እስከ 31 ሺ ብር ነበር።

ለዋጋው መቀነስ በባህረ ሰላጤው አገራት በተለይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለው ፍላጎት መቀዛቀዙ ነው።

በተለይ ከፍተኛ የወርቅ አስገቢ የነበረችው ዱባይ ፍላጎት በገዥ ደንበኞች መቀነስ ምክንያት መቀዛቀዙ ነው የሚነገረው።

የወርቅ ኮንትሮባንድ በተለያየ መንገድ ከአገር እንደሚወጣ ነው የሚነገረው በተለይ በምስራቅ ኢትዮጵያ አድርጎ በሶማሌላንድ በኩል ወደ ዱባይ የሚገባው ህገወጥ የወርቅ ምርት ከፍተኛ እንደሆነ ነው የሚገለጸው።

የዋጋው መቀዛቀዝ እንደ ነዳጅ መወደድ እና መጥፋት የመሰሉ ከምርት ሂደት እንቅፋቶች ጋር ተያይዞ ወርቅ የማምረት ሂደቱ በተለይ በመካከለኛ ደረጃ ለሚገኙ አምራቾች ሳቢ አለመሆን መጀመሩ ነው እየተገለፀ የሚገኘው።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories