የመንግስት ልማት ድርጅቶች ለሀገራዊ በጀት ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ድርሻ ለመሸፈን ማቀዳቸው ተገለጸ

​የመንግስት ልማት ድርጅቶች በተያዘው በጀት ዓመት ለሀገራዊ በጀት ከሚጠበቀው ድርሻ ውስጥ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ለመሸፈን ማቀዳቸው ተገለጸ።
​የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በገመገሙበት ወቅት እንዳስታወቁት፣ ድርጅቶቹ ከጥያቄ ምልክት ወጥተው ግዙፍ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ።

​ሰብሳቢው አክለውም፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ የመጣው ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ለዚህ ስኬት መሰረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋማቱ “ገቢ ካላመጣንና ትርፍ ካላስመዘገብን መኖር አንችልም” የሚል ጽኑ አቋም መያዛቸው የምርታማነት እድገቱ ዋና ሞተር እንደሆነ ገልጸዋል።
​በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ ሆልዲንጉ ስር የሚገኙ ተቋማት 277.49 ቢሊዮን ብር ግብር እና ቀረጥ በመክፈል የዕቅዳቸውን 111 በመቶ ማሳካት መቻላቸውን ተናግረዋል።
​በዚህም 22 የሆልዲንግሱ ተቋማት በታማኝ ግብር ከፋይነት ከገቢዎች ሚኒስቴር እውቅና ማግኘታቸው፣ ተቋማቱ ለፋይናንስ ግልጽነት እና ለሀገር ግዴታ መወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories