በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  የውጭ ምንዛሬ ጨረታ የባንኮች ፍላጎት ቀነሰ

By EBV Staff Writer

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  በሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ይፋ በተደረገው 24ኛው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤት የኢትዮጵያ ባንኮች በጨረታው ላይ ያሳዩት ተሳትፎና የጨረታ ዋጋ ከቀደመው ዙር ጋር ሲነጻጸር መቀነሱ ተስተውሏል።

በዚህ ዙር 14 ባንኮች ብቻ በጨረታው የተሳተፉ ሲሆን፣ በቀደመው ጨረታ 16 ባንኮች ተሳትፈው ነበር።

ብሔራዊ ባንኩ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለጨረታ ያቀረበ ሲሆን በባንኮቹ የቀረበው አጠቃላይ ጥያቄ 160.5 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል።


በጨረታዎች ከፍተኛ ሆኖ የቀረበው ዋጋ 157 ብር ለአንድ ዶላር ሲሆን፣፣ ዝቅተኛው ደግሞ 152 ብር ለአንድ ዶላር ቀርቧል። ከ14ቱ ተሳታፊ ባንኮች ውስጥ 9ኙ የውጭ ምንዛሬ ድልድል ማግኘት ችለዋል።


የጨረታው ውጤት ባንኮች ለውጭ ምንዛሬ ጨረታ ለመካፈል የሚያሳዩት ፍላጎት በትንሹም ቢሆን የቀነሰ ነው። ከቀደመው ጨረታ ጋር ሲነጻጸር ለአንድ ዶላር የቀረበው ከፍተኛ ዋጋ በ1 ብር ዝቅ ብሏል፤ ይህም በውጭ ምንዛሬ ገበያ ያለው የፍላጎት ጫና በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ መሆኑን ቢያሳይም፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት አሁንም ተግዳሮት ሆኖ እንደቀጠለ ያሳያል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories