ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ በሀገር ውስጥ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል፡፡
‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ፤ በሁለት ክፍሎች፣ በአምስት ምዕራፍ፣ በ 500 ገጽ ተሠናስሎ በ850 ብር ዋጋ ለገበያ ቀርቧል።
‹‹ብዕርና ባሩድ››፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስንክሳር በጥልቀት የሚዳስስ፣ በኢትዮጵያ የ 70 ዓመታት ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ ጉልህ ሚና የተጫወቱ፣ የአሥራ ስምንት አንጋፋ ፖለቲከኞችን ሃሳብ ‹‹ከፈረሱ አፍ›› በሚል ክፍል ስር እንደያዘም ተጠቁሟል፡፡
‹‹ብዕርና ባሩድ›› የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅጡ ለመረዳት ለሚሹ፣ ለተመራማሪዎችና ለሀገራቸው የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ለሚሹ በጥንቃቄና በሚዛናዊነት የቀረበ መጽሐፍ እነረደሆነ ተገልጿል፡፡
‹‹ብዕርና ባሩድ›› ቀደም ሲል በአውሮፓ በፍራንክፈርት፣ በርሊን፣ ሎንዶን፣ ስቶኮልም፣ ኦስሎ፣ ብራስልስ እና ስዊዘርላንድ በተጨማሪ በአሜሪካ ግዛቶችና በካናዳ ቶሮንቶ ለአንባቢያን ቀርቧል።
በአማዞንም፣ በሕትመት- በኪንድል (Paparback) እና በኢ-ቡክ (e-book) ታትሞ አንባቢዎች እንደሚያገኙት ተጠቁሟል።
አሁን ደግሞ ለሀገር ውስጥ አንባቢዎች በተለያዩ የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮችና በአዟሪዎች እጅ ለገበያ ቀርቧል፡፡SECO



