አሜሪካ ለኢትዮጵያ የስንዴ እና ማሽላ እርዳታ ላከች

የአሜሪካ መንግሥት ወደ 47,000 ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የምግብ እህል የጫነ የጭነት መርከብ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓዘ መሆኑን አስታወቀ። በ”ሰላም ለምግብ” መርሃ ግብር የተላከው ይህ እርዳታ 37,700 ቶን ማሽላ እና 9,200 ቶን ስንዴን ያካተተ ነው።

ይህ እርዳታ የተላከው የኢትዮጵያ መንግሥት በስንዴ ምርት ራሱን መቻሉን እና ወደ ውጭ መላክ መጀመሩን በተደጋጋሚ ከገለጸበት ማግስት ነው። ይሁን እንጂ፣ የአሜሪካ የግብርና መምሪያ በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎት በየጊዜው እያደገ በመሆኑ፣ ሀገሪቱ አሁንም ወደ 1.4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚጠጋ የስንዴ ምርት ከውጭ ማስመጣት እንደምትፈልግ ያሳያል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በግጭት፣ በመፈናቀል እና በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በኢትዮጵያ የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህ የአሜሪካ እርዳታ የሀገሪቱን የስንዴ ራስን የመቻል ጥያቄዎች እና የሰብአዊ ድጋፍ አስፈላጊነትን ዳግም አነጋጋሪ አድርጎታል።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories