የባህር ላይ ጥቃት በቀጠናው እያገረሸ መጤቷል

የታንዛኒያ ባንዲራ የምታውለበልብ መርከብ በባህር ዘራፊዎች መያዙ ተሰማ

የታንዛኒያ ሰንደቅ ዓላማ የምታውለበልበው “ኤምቲ አሳና” የተሰኘች የካርጎ መርከብ፣ በየመን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በባህር ዘራፊዎች ቁጥጥር ስር መዋሏ ተዘገበ። መርከቧ ከፓኪስታን ካራቺ ወደ ሶማሊያ ቦሳሶ በመጓዝ ላይ ሳለች ነበር ጥቃቱ የተፈጸመባት።

የባህር ደህንነት ተቋማት የሆኑት ዩኬኤምቲኦ እና አምብሬት እንደገለጹት፣ መርከቧ ከመጠለፏ ጥቂት ቀደም ብሎ የድረሱልኝ ጥሪ አስተላልፋለች። ይህ ክስተት ከ2023 መጨረሻ ወዲህ ዳግም እያገረሸ ባለው የባህር ላይ ዘረፋ ቀጣይ መሆኑ ተጠቁሟል። ሁኔታው በአደን ባህረ ሰላጤ እና በምዕራብ ህንድ ውቅያኖስ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረ ሲሆን፣ የደህንነት አካላትም አስፈላጊውን ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories