በአፍሪካ አህጉር እየታየ ባለው ፈጣን የቴክኖሎጂ መስፋፋት ሳቢያ የሳይበር ወንጀሎች እያደረሱት ያለው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ኢንተርፖል ይፋ አደርጓል።
አዲስ በተለቀቀው የኢንተርፖል የአፍሪካ የሳይበር ስጋት ግምገማ ሪፖርት መሠረት፣በአህጉሪቱ በሳይበር ወንጀል የሚደርሰው ቀጥተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ወደ 5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አድጓል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ 36 የአፍሪካ አባል ሀገራትን መረጃ መሠረት ያደረገው ይህ ሪፖርት፣ የዲጂታል መስፋፋቱ ፍጥነት ከሳይበር ደህንነት ዝግጁነት እጅግ የሰፋ መሆኑን ያሳያል። አህጉሪቱ የሞባይል ተጠቃሚዎቿ ቁጥር ከ1.1 ቢሊዮን በላይ ቢደርስም፣ የሳይበር ወንጀለኞች አርቴፊሻል ኢንተለጀንት (AI) እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥቃቶቻቸውን ይበልጥ አጠናክረዋል።
በሪፖርቱ መሠረት፣ በሳይበር ወንጀል የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ከ35,000 ወደ 87,000 አድጓል፤ የፋይናንስ ኪሳራም በእጥፍ ጨምሯል።
በግኝቱ የተረጋገጠው የገንዘብ ኪሳራ ከ192 ሚሊዮን ወደ 484 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል። በወንጀሉ የተጎዱ ሰዎች ቁጥርም ከ35,000 ወደ 87,000 ከፍ ብሏል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንት ለአጭበርባሪዎች ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ፣ ከአፍሪካ የሳይበር ወንጀሎች ከ55 በመቶ በላይ የሚሆኑት በቴክኖሎጂው አማካኝነት እንደሚፈጸሙ ተመላክቷል።
በምሥራቅ አፍሪካ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት በሞባይል ገንዘብ ማጭበርበር፣ በቴሌኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ጥሰት እና በክፍለ ሀገር አቀፍ ደረጃ ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን በሚያነጣጥሩ የራንሰምዌር አደጋዎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ።
የሕግ አስከባሪ አካላት ከቴክኖሎጂው ፍጥነት ጋር አብረው ለመጓዝ ገደቦች እንዳሉባቸው የጠቆመው ሪፖርቱ፤ 94 በመቶ የሚሆኑት ተቋማት በቂ የዲጂታል ፎረንሲክ መሣሪያዎች እንደሌሏቸው፣ 78 በመቶዎቹ ደግሞ የበጀት እና የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት እንዳለባቸው አሳይቷል።seco


