የምስራቅ አፍሪካን የንግድ መስመር ከሆኑት ዋና ዋና ማዕከላት አንዱ በሆነው የሞምባሳ ወደብ ውስጥ የዲዝል መኪኖችን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የመተካት አዋጭነት የሚያጠና አዲስ መርሃ ግብር ሊጀመር ነው። ይህ እርምጃ የተወሰደው በኮሪደሩ ላይ ያለው የጭነት ማጓጓዣ መጠን እያደገ በመምጣቱና ተያያዥ የሆነው የካርቦን ልቀት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነዉ ተብሏል።
ለዚህ ስራ ስኬት የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ መርሐ ግብር 190,000 ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል ። በጥናቱ ሰፊ ተሳትፎ ከሚያደርጉት መካከል የሰሜኑ ኮሪደር የትራንስፖርት አስተባባሪ አካል እና የኬንያ ወደቦች ባለስልጣን ይገኙበታል።
ጥናቱ በወደቡ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን በኤሌክትሪክ አማራጮች ለመተካት ያለውን ቴክኒካዊ አዋጭነት ይመረምራል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ጥናት የምስራቅ አፍሪካን የንግድ መስመር ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለማዘጋጀትና እስከ 2050 የተጣራ የካርቦን ልቀት መጠን ወደ ዜሮ ለማድረስ ለታለመው አረንጓዴ የትራንስፖርት ስትራቴጂ መሰረት የሚጥል ነዉ ተብሏል።seco


