አማራ ባንክ የቁጠባ ወለድ ምጣኔን እስከ 9 በመቶ አሳደገ

ኢትዮጵያ እየተገበረችው  ባለው የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ የባንኮች የቁጠባ ማሰባሰብ ውድድር እየጨመረ ነው።

ምስረታውን ከአራት አመት በፊት ያደረገው  አማራ ባንክ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን የቁጠባ ወለድ ምጣኔ ከፍ በማድረግ እስከ 9 በመቶ የሚደርስ ዓመታዊ ወለድ ማቅረብ ጀምሯል።
የባንኩ አዲሱ የወለድ ምጣኔ በተቀማጭ የገንዘብ መጠን ላይ የተመሰረተ ሲሆን እስከ 500 ሺህ ብር የሚደርስ ቁጠባ ላላቸው ደንበኞች 7.5 በመቶ፣ ከ500 ሺህ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ለሚያስቀምጡ 8 በመቶ እንዲሁም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ለሚያስቀምጡ ደግሞ 9 በመቶ ዓመታዊ ወለድ እንደሚሰጥ ነው ያስታወቀው።


የአማራ ባንክ ውሳኔ የመጣው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው የብሔራዊ ባንክ ምጣኔን ከ15 በመቶ ወደ 16 በመቶ ካሳደጉ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው።

የብድር ዕድገት ገደቡ መነሳቱ ባንኮች ተጨማሪ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲያሰባስቡ እና የብድር አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የሚገፋፋ መሆኑ ተገልጿል።
አማራ ባንክ ከ164 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች እንዳሉትና ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እንዳለው ይታወቃል።


አዲሱ የቁጠባ ወለድ ምጣኔ የመጣው ብሔራዊ ባንክ ለዓመታት ተግባራዊ ያደረገውን የዝቅተኛ የተቀማጭ ወለድ ምጣኔ መስፈርት ካነሳ በኋላ ነው። ይህም የግል ባንኮች ለተቀማጮቻቸው የሚሰጡትን የወለድ መጠን በበለጠ ነፃነት እንዲወስኑ ዕድል ሰጥቷል።
ቀደም ሲል ብሔራዊ ባንክ በጥቅምት 2017 የቁጠባ ሂሳብ ዝቅተኛ ወለድን ከ5 በመቶ ወደ 7 በመቶ ከፍ አድርጎ ነበር።

የዘርፉ ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ቢዝነስ ቪው  እንደገለጹት  የገንዘብ ፖሊሲውና የተቀማጭ ወለድ አወሳሰን ለውጦች ለኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ ይከፍታሉ። ባንኮች የገንዘብ ምንጫቸውን ለማጠናከርና የብድር ዕድገት ገደቡ መነሳቱን በመጠቀም ብድር ለማስፋፋት ሲሞክሩ፣ የተቀማጭ ገንዘብ ለማሰባሰብ ያላቸው ውድድር የበለጠ ሊጠናከር ይችላል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔውን (National Bank Rate) ወደ 16 በመቶ ያሳደገ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን አነስተኛ የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ መስፈርትም ሰርዟል።
 
ይህ እርምጃ የባንክ ኢንዱስትሪው ወደ ከፍተኛ ውድድር እና በገበያ መርህ ወደሚመራ አሰራር እንዲሸጋገር አድርጓል።


የአማራ ባንክ አዲስ የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ምጣኔ በደረጃ የተከፋፈለ ሲሆን፣ ከፍተኛ ተቀማጭ ላላቸው ደንበኞች የተሻለ ጥቅም ይሰጣል፡፡seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories