የቻይና ግሪን ኢነርጂቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው “ኤንቪዥን ግሩፕ” በሰሜናዊ ቻይና ሞንጎሊያ ክልል የገነባውን የ12.8 ጊጋዋት ሰዓት ግዙፍ የባትሪ ኢነርጂ ማከማቻ አውታር ሙሉ በሙሉ ከኃይል ማስተላለፊያ መረብ ጋር ማገናኘቱን አስታወቀ።
ይህ አውታር የከርሰ ምድር እና የባትሪ አጠቃቀምን በ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ የሚቆጣጠር ሲሆን፣ 4 ጊጋዋት ሰዓት አቅም ያለው “ቻጋን ሃዳ” የተሰኘው ማዕከሉ የዓለም ትልቁ ነጠላ የኤሌክትሮኬሚካል ኢነርጂ ማከማቻ ጣቢያ ሆኗል።
የዘመናዊው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የቀን የኤሌክትሪክ ዋጋ ንረትንና የፍላጎት ትንበያዎችን በማጥናት የኃይል ስርጭቱን በራሱ ያቀናጃል። ይህም የባትሪዎችን የዕድሜ ልክ ገቢ ከቀድሞው የተለመደ አሰራር ጋር ሲነጻጸር በ20 በመቶ እንደሚያሳድገው የኩባንያው መሐንዲሶች ገልጸዋል።
በክልሉ የሚመነጩት እንደ ንፋስ እና ፀሐይ ያሉ ታዳሽ ኃይሎች ከፍላጎት በላይ ሲሆኑ ይህ ማዕከል ትርፍ ኃይሉን በማከማቸት ለከፍተኛ የኃይል ፍጆታ ሰዓታት ያስተላልፋል ተብሏል።seco


