ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት 20 ሺህ ብር ተሻግሮ የነበረው ሰሊጥ በኩንታል 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ
በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በየቀኑ በሚደረገው ጨረታ ላይ በተለየው አመላካች ዋጋ የሰሊጥ ምርት በኩንታል ለመጀመሪያ ጊዜ 21 ሺህ ብር ተሸጧል፡፡
ምንም እንኳን በዚህ የክረምት ወቅት የምርት ዋጋ ጭማሪ ማሳየት የተለመደ ቢሆንም የዘንድሮው ጭማሪ ግን እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ነው ባለሞያዎች የገለጹት፡፡
በዚህ መሰረት ትላንት ረዕቡ ነሐሴ 6 ቀን 2018 በነበረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጨረታ ላይ የወለጋ ሰሊጥ በኩንታል 17 ሺህ ብር ሲሸጥ በአለም ገበያ በጥራቱ በጣም ተፈላጊ የሆነው የሑመራ ጎንደር ሰሊጥ በኩንታል 21 ሺህ ብር ሊሸጥ ችሏል፡፡
በዚሁ በጀት አመት መስከረም ወር ላይ 19 ሺህ ብር ተሸጦ የነበረ ሲሆን ባለፉት ወራት ደግሞ በአማካኝ 18 ሺህ ብር ሲሸጥ ቆይቶ አሁን ላይ በኩንታል 21 ሺህ ብር ማውጣት ችሏል፡፡
አምና በዚህ ወቅት 17 ሺህ 500 ብር አካባቢ መሸጡ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ የተመዘገበው ዋጋ ከቀደመው ዓመት 20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ሐምሌ 22 ቀን 2016 ከተጀመረ በኋላ የሑመራ ጎንደር ሰሊጥ በአማካነካኝ 14 ሺህ ብር አካባቢ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ከቀዳሚ ወጪ ሸቀጦች አንደኛው የሆነው ሰሊጥ በጸጥታ ችግር ምክንያት በበቂ ሁኔታ ለገበያ እየቀረበ አይደለም ሲሉ ላኪዎች እና ባለሞያዎች ስጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡
ቀደም ሲል በአፍሪካ በዘርፉ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ቀዳሚ አምራች ላኪዎች የነበሩ ቢሆንም በተለይ ምርት እና ምርታማነታቸውን እያሳደጉ የመጡ አዳዲስ አምራች አገራት ለኢትዮጵያ ገበያ ከፍተኛ ስጋት እንደሆኑ ነው በባለሞያዎቸች የሚገለፀው፡፡
አሁን ላይ በቀጠናው ባለው የፀጥታ ሁኔታ የሰሊጥ ምርት ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ ነው የዘርፉ ባለሞያዎቸች ለኢቢቪ የገለጹት፡፡seco


