ተቋሙ Digital ESL ”የደንበኛ ራስ አገዝ ዲጂታል አገልግሎት (Customer Self Service Web & Mobile App) በይፋ አስመርቋል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የአገልግሎት አሰጣጡን ሙሉ በሙሉ ዘመናዊና ፈጣን የሚያደርገውን ”Digital ESL”የደንበኛ ራስ አገዝ ዲጂታል አገልግሎት (Customer Self Service Web App) በይፋ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ችሏል።

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አብዱልበር ሸምሱ በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት መተግበሪያው ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል ስልካቸው ወይም በዌብ ፖርታሉ አማካኝነት ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በፍጥነትና በሙሉ ግልጽነት ማግኘት የሚችሉበትን ዘመናዊ አሰራርን የዘረጋ ነው፡፡
መተግበሪያው ቀደም ሲል የነበረውን አላስፈላጊ የደንበኞች የጊዜ ብክነት እና ወጪ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል ተብሎለታል ።
ከዚህም በተጨማሪ ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት ከሰው ንክኪ ነፃ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ነው የተባለው፡፡SECO


