ሲጠበቅ የነበረው የአኪር ኮንስትራክሽን ሃራጅ ታገደ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበለት የመቃወም አቤቱታ መሰረት ስመ ጥር የሆነው አኪር ኮንስትራክሽን ላይ እሮብ ነሀሴ 27 ቀን ሊደረግ የነበረው የሃራጅ ጨረታ ተሰርዟል፡፡

የአኬር ኮንስትራክሽን ባለቤት የነበሩት አቶ አወጣኸኝ ኪሮስ ቀደም ሲል ሲያስተዳድሩት የነበረውን ግዙፍ የግንባታ ተቋም ከነ ጥቅሞቹ እና ንብረቶቹ ለ ሰይፉ አምባዬ እና ይኩኖአምላክ አምባዬ የሸጡ ቢሆንም ገዥዎች በውላቸው መሰረት ለሻጭ መክፈል የነበረባቸውን የመግዣ ሙሉ ገንዘብ ሳይከፍሉ በመቅረታቸው ጉዳዩ ወደ ክስ አምርቶ ነበር፡፡

ይህንንም ተከትሎ ከሳሽ አቶ አወጣኸኝ አኬር ኮንስትራክሽን ድርጅቱ በሃራጅ ተሸጦ ቀሪ ገንዘባቸውን እንዲወስዱ መፈረዱን ተከትሎ ሃራጁ ለእሮብ ሲጠበቅ ነበር፡፡

ሆኖም በእለቱ ጨረታው እግድ ስለወጣበት መከናወን እንዳልቻለ ነው ኢቲ ቢዝነስ ቪው ያገኘችው የፍርድ ቤት ትእዛዝ የሚያሳየው፡፡

በፍርድ ቤት ትእዛዝ መሰረት እግዱ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው ባለፈው ነሃሴ 22 ቀን በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖረት እና ሎጅስቲክ የቀረበው የመቃወም አቤቱታ ነው፡፡

ግዙፉ መንግስታዊ የሎጅስቲክ ኩባንያ ባቀረበው የመቃወም ማመልከቻ አቤቱታ እንደተጠቀሰው ኩባንያው ከአኪር ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የፍርድ ቤት ክርክር አድርጎ ውሳኔ እንደተሰጠው እና በአፈጻጸም ላይ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡

በመሆኑም ሃራጁ ተደርጎ የግንባታ ድርጅቱ የሚሸጥ ከሆነ በባህር ትራንስፖረት ኩባንያው ላይ የማይተካ ጉዳት ይደርሳል ሲል ነው ሃራጁ እንዲታገድ አቤት ያለው፡፡

ሆኖም የፍርድ ባለ መብት የሆኑት (አወጣኸኝ ኪሮስ) በጨረታው አሸናፊ የሆነ ወገን የማህበሩን መብት እና ግዴታ የሚወርስ እና የሚያስቀጥል እንደመሆኑ የሃራጅ ሂደቱ እንዲቀጥል ነሃሴ 25 ቀን በሰጡት ምላሽ የይታገድ ሃሳቡን ተቃውመው ነበር፡፡

በተመሳሳይ የፍርድ ባለ እዳ የሆኑት (እነ ሰይፉ እና ይኩኖአምላክ አምባዬ) ነሃሴ 25 ባቀረቡት አስተያየት የባህር ትራንስፖርት ድርጅቱ የእግድ ጥያቄ ተገቢ ነው ማለታቸው ነው የታወቀው፡፡

ቀደም ሲል ባለ እዳዎች ነሃሴ 21 ቀን በተጨማሪነት ባቀረቡት አቤቱታ የሚሸጠው ድርጅት አክሲዎኖች ወቅታዊ ዋጋ ተገምቶ ሃራጁ እንዲወጣ አቤት ማለታቸው ነው የተጠቀሰው፡፡

የልደታ ከፍተኛ ፍረድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ የባህር ትራንስፖርት የጨረታ ይታገድልኝ ጥያቄ ታይቶ መልስ እስኪሰጥ ሃራጁ እንዲታገድ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የፍርድ ባለ እዳዎች አቤቱታ የሃራጅ መቃወም አቤቱታ በፍርድ ቤቱ እልባት እስኪያገኝ ሊታይ የሚችል መሆኑ ጠቅሶ አቤቱታውን መቀበል አላስፈለገም ብሏል ከፍተኛው ፍርድ ቤት፡፡

በመሆኑም የአኪር ኮነስትራክሽን ጨረታ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱ ግልጽ ሆኗል፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከሪፖርተሩ ዘጋቢ ዳዊት ታዬ ጋር ቆይታ የነበራቸው አቶ አወጣኸኝ ኪሮስ በራሳቸው እና የአባታቸው የላቲን ፊደል መነሻ የሰየሙትን አኪር ኮንስትራክሽን በሃራጁ በመሳተፍ ድጋሚ በእጃቸው ለማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጠው ነበር፡፡

ከ40 አመት በፊት ግድም የተቋቋመው አኪር እጅግ ግዙፍ እና በርካታ የግንባታ ስራዎችን ማከናወን ቢችልም ባጋጠመው ድንገተኛ የፋይናንስ እጥረት የኩባንያው ባለቤት ሊያስቀጥሉት ይችላሉ ብለው ላመኑባቸው ሁለት ወንድማማቾች የዛሬ 10 አመት ግድም ነበር የሸጡት፡፡ ሆኖም ከሽያጭ ስምምነት በኋላ ይገባቸው የነበረው ገንዘብ ስላልተሰጣቸው ወደ ክስ ማምራታቸውን ነው የገለጹት፡፡

አቶ አወጣኸኝ ከዚህ ቀደም ይፎካከሯቸው ከነበሩ ጥቂት የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች መካከል አንዱ በሆነው ዲኤምሲ ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡SECO   

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories