የኢትየጵያ ንግድ ባንክ በባንኩ የሞባይል መላ/አፕ ማስተላለፍ የሚቻለውን የእለት የገንዘብ መጠን 150 በመቶ አሳደገ፡፡
ካለፈው ሳምንት መጨረሻ አንስቶ ተግባራዊ እንደተደረገ የታወቀው አዲሱ አሰራር ማንኛውም ግለሰብ ደንበኛ በቀን እስከ 1.5 ሚሊየን ብር ማስተላለፍ እንደሚችል ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም ግለሰብ ደንበኞች በአንዴ እስከ 400 ሺ ብር ድረስ ወደሌላ ሰው ሂሳብ ማስተላለፍ የሚችሉ ሲሆን በጠቅላላው እስከ አንድ ሚሊየን 500 ሺ ብር ድረስ ማስተላለፍ እንደሚችሉ ተገልጧል፡፡
ቀደም ሲል ግለሰብ ደንበኞች በአንዴ 300 ሺ ብር እንዲሁም በቀን ማስተላለፍ የሚችሉት 600 ሺ ብር ብቻ ነበር፡፡
በኢትዮጵያ የባንኮች የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር በከፍተኛ መጠን እያደገ እንደመጣ ነው የሚገለጸው፡፡ በቅርብ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በአመት እስከ 33 ትሪሊየን ብር ሞባይል አፖችን ጨምሮ በዲጂታል መላ ተላልፏል፡፡
የንግድ ባንክ አመታዊ ኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሲቢኢ ብር እና ኢንተርኔት ባንኪንግን ጨምሮ የዲጂታል መላ የገንዘብ ዝውውር 22 ትሪሊየን ብር ደርሷል፡፡ SECO


