ኢትዮጵያ 38 ሚሊዮን የእግር ኳስ ደጋፊዎች እንዳሏት ጥናት አመለከተ


– ስለ ኳስ ሰርች የሚያደርገው ቁጥር ከፍ ያለ ነው


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የእግር ኳስ ፍላጎት ካላቸው አገራት መካከል ብትገኝም፣ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾቿ ቁጥር ከደጋፊዎቿ መጠን ጋር ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው የ2026 ጥናት አመለከተ።


በእግር ኳስ የትንበያ መላ የሆነው ‘The Daily Punt’ የአለም ዋንጫ እየተደረገበት በነበረበት በሐምሌ ወር ያካሄደው ጥናት፣ በ10 የአፍሪካ አገራት ያለውን የእግር ኳስ ተሳትፎ የደጋፊዎች ቁጥር፣ የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች፣ የተመዘገቡ ክለቦች እና የእግር ኳስ ፍለጋዎችን (ሰርች) በመመርመር አወዳድሯል።


በጥናቱ መሠረት ኢትዮጵያ 38 ሚሊዮን የእግር ኳስ ደጋፊዎች እንዳሏት ተገልጿል። ይህም ናይጄሪያ አሏት ከተባለው 82.44 ሚሊዮን በኋላ በጥናቱ ከተካተቱት አገራት መካከል ከፍተኛ የደጋፊ ቁጥር ነው።


ኢትዮጵያ በአንድ ወር 20.39 ሚሊዮን የእግር ኳስ ጉዳዮች የተያያዙ የኢንተርኔት ፍለጋዎችን አስመዝግባለች። ይህም በአገሪቱ ያለውን የእግር ኳስ ፍላጎት መጠን ያሳያል ነው የተባለው።


በሌላ በኩል ጥናቱ ኢትዮጵያ 114 ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች እና 50 የተመዘገቡ የእግር ኳስ ክለቦች እንዳሏት ያሳያል። ይህ ቁጥር ከአገሪቱ ያለው ከፍተኛ የደጋፊ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር የፕሮፌሽናል እግር ኳስ መሠረተ ልማት ስፋት እና የደጋፊዎች ብዛት መካከል ልዩነት መኖሩን ያመለክታል ሲል ጥናቱ በትንተና ጠቅሷል።


በአጠቃላይ ኢትዮጵያ 29 ነጥብ በማግኘት 10ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ጥናቱ አስታውቋል።

ደቡብ አፍሪካ 100 ነጥብ በማግኘት ቀዳሚ ስትሆን፣ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ ተከትለዋል።

ኬንያ፣ ጋና፣ ሴኔጋል፣ ካሜሮን፣ ኮት ዲቯር እና ጊኒ በመለኪያው ከ4ኛ እስከ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ኢትዮጵያን ይቀድማሉ፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories