ዘመን ባንክ አጠቃላይ ሀብቱ 116 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታወቀ


ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት
6.75 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አስመዝግቧል


በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
ዘመን ባንክ የባለአክሲዮኖች 18ኛ መደበኛ እና 13ኛ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ዘበነ እንዳስታወቁት ባንኩ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 9.97 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ትርፍ ማስመዝገብ ሲችል አጠቃላይሀብቱም በ31 ነጥብ 3 በመቶ በማደግ ወደ116 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል፡፡

የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 14.3 ቢሊዮን ብር እና ጠቅላላ ካፒታሉ ወደ 26 ቢሊዮን ብር መድረሱን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዘርፉ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች ሲገመገም፣ የባንኩ ውጤቶች በዘርፉ ከሚታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች መካከል ሆኖ እንደሚገኝ ነው ያስታወቁት፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ ከ14 ቢሊየን ብር በላይ አጠቃላይ ገቢውም 17.9 ቢሊየን ብር መድረሱና 6.75 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 142 ማሳደጉን ጠቁመው የባንኩ አጠቃላይ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውር ብር 68.87 ቢሊየን መድረሱን አስታውቀዋል፡፡SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories