የባንኩ የ2019 ዓ.ም የደንበኛ አገልግሎት ሳምንትን ሲጀምር የመጀመሪያውን የአዲስ አበባ ኮርፖሬት ቅርንጫፍ መርቆ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡
የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ይህንዓለም አቅናው እንደገለጹት የኮርፖሬት ቅርንጫፍ ሥራ መጀመር ቅርንጫፍ ምደባ ብቻ ሳይሆን የባንኩን የደንበኛ ተሞክሮ፣ የአገልግሎት ጥራትና የንግድ አጋርነት ወደ ቀጣይ ደረጃ ለማሸጋገር እየተወሰደ ያለው ስትራቴጂያዊ እርምጃ ያሳያል፡፡
አዲሱ ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ለኮርፖሬትና ለኮሜርሻል ደንበኞች የተሻለ የግንኙነት አስተዳደር፣ ፈጣን ምላሽ፣ ግልጽ መረጃ፣ የንግድ ፍላጎትን የሚረዳ ምክርና ተስማሚ የባንክ መፍትሔዎችን ለማቅረብ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
የ2019 ዓ.ም የደንበኛ አገልግሎት ንቅናቄንም በአንድ ሳምንት ጥሩ አገልግሎት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ የደንበኛን ድምፅ ለመስማት፣ ችግሮችን ለመለየት እና ተጨባጭ ማሻሻያዎችን ለመጀመር የተዘጋጀ የለውጥ መነሻ እንደሆነ ነው ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።SECO


