ዘመን ባንክ  698 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ አስመዘገበ

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠን 52 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ደረሰ

የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ ቢምር እንዳስታወቁት ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት ጠንካራ የፋይናንስ አፈጻጸምና ቀጣይነት ያለው እድገት ያስመዘገበበት ነው፡፡

የባንኩ አጣላይ የብድር መጠን 52 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቁመው የብድር መጠኑ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ10 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወይም የ24 በመቶ ዕድገት እንዳስመዘገበ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ብሔራዊ ባንክ ካስቀመጠው የ24 በመቶ የብድር ዕድገት ጣሪየ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ የተከናወነ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በበጀት አመቱ ባንኩ ውጠታማ ከሆነባቸው ዘርፎች የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንደሆነ የተናገሩት ወ/ሮ እንዬ ባንኩ በተጠናቀቀወ በጀት አመት 698 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማመዝገባ የዕቅዱን 102 ነጥብ 5 በመቶ ብልጫ እንዳስመዘገበ ተናግረዋል፡፡

ከተገኘው ገቢ ውስጥም የወጪ ንግድ 51 ነጥብ 1 በመቶ፣የገቢ ሀዋላ 33.9 በመቶ፣ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ጨረታ 10 ነጥብ 61 በመቶ፣ የአለም አቀፍ  ካርድ ግብይት ደግሞ 3 ነጥብ 15  በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ባንኩ በውጭ ምንዛሬ ግኝት ባሳየው አፈጻጸም ከግል ባንኮች አራተኛ ደረጃ መያዝ እንደቻለ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እንዬ አስታውቀዋል፡፡SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories