የዘመን ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፍሬህይወት አለማየሁ እንደገለጹት ማህነሩ በሸሪዓ መርሆዎች ላይ የተመሰረተውን «ኢማኔ ተካፉል» አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
«“ኢማኔ” እምነት፣ ታማኝነት እና ጽናት የሚለውን ሲወክል “ተካፉል” ደግሞ “አንዱ ለሌላው ዋስትና መሆን”፣ የመረዳዳትና የጋራ ኃላፊነት መገለጫ ነው።
“ኢማኔ ተካፉል” በወካላ-ሙዳራባ መርህ ላይ በመመሥረት፣ በእምነቱና በሥነ-ምግባር መርሆዎች ላይ የተመሠረተ አቃፊ የፋይናንስ አገልግሎትን የሚያረጋግጥ እንደሆነ ተጠቁሟል።
የ«ኢማኔ ተካፉል» አገልግሎታችን ሙሉ በሙሉ በሸሪዓ ሕግና መርሆዎች የተቃኘ እና በነጻ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ተመርምሮና ጸድቆ የቀረበ ነው።
አሰራሩም ግልጽነት ባለው መልኩ የተካፉል ፈንድ እና የኦፕሬተሩ ፈንድ ሙሉ በሙሉ የተለያዩ የባንክ ሂሳቦችና መዝገቦች ያሏቸው እንዲሆኑ ተደርጎ መዋቀሩ ተገልጿል።
አገልግሎቱም ለንግዱ፣ ለአምራቹ፣ ለትራንስፖርት፣ ለኮንስትራክሽን፣ ለወለድ አልባ ባንክ (IFB) ደንበኞች እና ለግል ተገልጋዮች አጠቃላይ የዋስትና ሽፋን ይዞ ቀርቧል።
አገልግሎቱም በሁሉም ቅርንጫፎች እንደሚሰጥ ተነግሯል።SECO


