ከ9 ሺህ 800 በላይ የሳይበር ጥቃት ተሞክሯል

የኢትዮ ቴሎኮም  ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር አቶ እንዳለ አስራት እንደገለጹት በየዕለቱ በበሚደረግ  የዲጂታል አጠቃቀም ውስጥ የሳይበር ደኅንነትን  ቋሚ ልማድ አድርጎ ማካተት ይገባል፡፡
 
ኩባንያው ዲጂታል ኢትዮጵየ 2030 እውን ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ብለው በሚሊየን ለሚቆጠሩ ደንበኞቹ የኮሚኒኬሽን፣ለኢንተርፕራይቾች ሶሎሽን እና የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት  እያቀረበ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
 
የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ደህንነቱ የተጠበቀና አስታማማኝ በማድረግ የደንበኞቹን እምነት እየጠበቀ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
በ2018 በበጀት አመት በካምፓኒው ላይ 9 ሺህ 800 የሚደርሱ የሳይበር ጥቃት  መሞከሩን የተናገሩት አቶ እንዳለ የተቃጡ ጥቃቶችን የተቋሙ የደህንንት ቡድን ቀድሞ በማወቅና በመለየት ርምጃ በመውሰድ መከላከል እንደተቻለ አስታውቀዋል፡፡

የደህንነት ኦፕሬሽን ቡድን 24 ሰዓት ችግሮችን በመለየት ርምጃ እየወሰደ የደንበኞችን ደህንነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል፡፡
ካምፓኒው ሆራይዘን 20226 ላይ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት በተመለከተ ከዳታ ብሪጅ ጋር  ጥናት ያከናወነ ሲሆን 48 በመቶ ተጋላጭነት ከሶስተኛ ወገን  ሲስተሞችና ኮሚኒኬሽን  ጋር የሚደረግ ግንኙነት እንደሆኑ በጥናት መረጋገጡን አስታውሰዋል፡፡
 
 
በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉትን የዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅዶች በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ስነ-ምኅዳር መገንባት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
 
በኢትዮቴሌኮም የሳይበር ደህንነት ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ጀማል መሐመድ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የዲጂታል ስርዓት እየተስፋፋ እንደመጣ ጠቁመው ይንን ተከትሎ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ስራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
 
ለሳይበር ደህንነት ተጋላጭ ከሆኑ ተቋማት መካከል የጤና፣የምርምር ማዕከላትና አገልግሎት ሰጪተቋማት እንደሚገኙበት ተናግረው የሳይበር ደህንነትን የዘወትር ልማድ በማድረግ መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡
 
የካምፓኒው የኮርፖሬት ጉዳዮች እና ኮሙኒኬሽን ቺፍ ኦፊሰር አቶ መሳይ ውብሸት ኢትዮ ቴሌኮም እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን የዲጂታል አገልግሎት ፍላጎት ከማሟላት ጎን ለጎን፣ ለደንበኞቹ ደኅንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ የመሠረተ ልማት አገልግሎቶችን በማቅረብ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
 
ኩባንያው በ“ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ ትግበራ ወቅት የሳይበር ደኅንነትን በየዕለቱ በሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ እንደ ቋሚ ልማድ በማካተት፣ የደኅንነት ስርዓቶቹን የማጠናከርና ደንበኞቹን ከሳይበር ስጋቶች የመጠበቅ ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
 
የዘንድሮው የሳይበር ደህንነት ወር ሕፃናትን ከበይነ-መረብ ጥቃትና ተጋላጭነት ለመጠበቅ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence – AI) አማካኝነት የሚመጡ አዳዲስ የሳይበር ጥቃቶችን መከላከልና ዝግጁነትን ማሳደግ፣ የቁልፍ መሠረተ ልማት ጥበቃ: የዲጂታል 2030 ሀገራዊ ግብን ለማሳካት የመንግስትና የግል ተቋማትን የመከላከል ብቃት ማጠናከር ዋና ዋና ትኩረቶች ናቸው፡፡
 
ዜጎች የኢንተርኔት አጠቃቀም ወቅት ጠንካራና ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል (Password) መጠቀም፣ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (MFA/2FA) መጠቀም፣የማጭበርበሪያ መልዕክቶችን  መለየትና አለመንካት እንዲሁም ሶፍትዌሮችንና መተግበሪያዎችን በወቅቱ በማዘመን የደህንነት ክፍተቶችን በመድፈን የሳይበር ጥቃትን መከላከል ይቻላል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories