በጥቅምት ወር የምግብ ምርቶች 15.1 በመቶ ዋጋ ጭማሪ አሳዩ

የጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.6 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ  ሲሆን 2018 ዓ.ም መስከረም ወር ከነበረው 11.6 በመቶ ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ አሳይቷል።

የምግብና አልኮል ያልሆኑ መጠጦች ዋጋ 14.1 በመቶ ሲጨምሩ በዋናነት አትክልት 11.1 በመቶ ፣ ስጋ 23.8 በመቶ ወተት፣ የወተት ተዋፅኦዎች እና እንቁላል 20.1 በመቶ ፣ ፍራፍሬ 11.1 በመቶ፣ ዘይት እና ቅቤ 20.6 በመቶ ስኳር ፣ ማር እና ቸኮሌት 36.2 በመቶ እና ዳቦ እና እንጀራ 10.7 በመቶ ፣ የምግብ ምርቶች 15.1 በመቶ በመጨመራቸው የተመዘገበ ጭማሪ እንደሆነ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያስታወቀው፡፡

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 15.4 በመቶ የደረሰ ሲሆን ትራንስፖርት 17.1 በመቶ፣ አልኮል መጠጦችና ትምባሆ 18.92 በመቶ፣ በኮሙዩኒኬሸን 9.1 በመቶ ፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች 11.1 በመቶ ትምህርት 15.5 በመቶ ፣ ጤና 10.5 በመቶ እንዲሁም ሌሎች እቃዎችና አገልግሎቶች 19.1 በመቶ ሆነው ተመዝግበዋል። SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories