የተሻሻለው የፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ ደንብ ቁጥር 597/2019 ከጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ·ም ጀምሮ በስራ ላይ ውሏል።
በደንቡ ድንጋጌ መሰረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ከ50 ሺህ ብር በላይ ገቢ የሚያገኝ ማንኛውም ግለሰብ ግብር የመክፈል ግዴታ አለበት።
በዚህም ዓመታዊ ገቢያቸው ከ50 ሺሕ ብር በላይ የሆኑ የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች 15 በመቶ ግብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
በአዋጁ መሠረት፤ በዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ባለቤት የሆኑ ግብር ከፋዮች ገቢያቸውን አሳውቀው እያንዳንዱ ሩብ ዓመት በተጠናቀቀ በ30 ቀናት ውስጥ ግብር መክፈል አለባቸው።
በአንድ ዓመት ውስጥ የተገኘው ገቢ ከ50ሺህ ብር የማይበልጥ ከሆነ ደግሞ ቀደም ሲል የተከፈለው ግብር ለወደፊት ከሚከፈለው ጋር እንዲካካስ ወይም ተመላሽ እንደሚሆን በደንቡ ላይ ሰፍሯል።
የዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የማውጣት ግዴታ የተጣለባቸው ሲሆን ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ግብር ተቀናሽ በሚደረግበት ጊዜ እንደሌሎች የንግድ ዘርፎች የንግድ ፈቃድ እንዲያቀርቡ ሳይገደዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራቸውን ብቻ ያቀርባሉ።
የንግድ ስራ ገቢ ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ምንጮች ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ያገኘውን ሁሉንም የገቢ መጠን (በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት ያገኘውን) በሚመለከት፣ ትክክለኛና የተሟላ የሂሳብ መዝገብ መያዝ አለበት።SECO


