የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  ፍሬሕይወት ታምሩ የአፍሪካ ዲጂታል መሠረተ ልማት መሪዎች ውስጥ ተካተቱ

 የቀድሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚና በአሁኑ ወቅት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ፍሬሕይወት ታምሩ በአፍሪካ የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ 100 ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።

ይህ አህጉራዊ እውቅና በአፍሪካ ሃይፐርስኬለርስ (Africa Hyperscalers) እና ዘ ሊትልስቴፕስ ግሩፕ (The Littlesteps Group) ይፋ የተደረገ ሲሆን ሚኒስትሯ በቴሌኮም እና በመሰረተ ልማት ዘርፍ ግንባር ቀደም ሆነው የተመረጡት ኩባያችንን በማዘመን እና በማሳደግ ላሳዩት የላቀ አመራር ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ፍሬህይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ለስምንት ዓመታት ተቋሙን የመሩ ሲሆን በቆይታቸው የኩባንያውን ደንበኞች ቁጥር ወደ 90.1 ሚሊዮን በማሳደግ፣ የ5ጂ (5G) አገልግሎትን በማስጀመር እና ቴሌብርን (telebirr) ወደ ሥራ በማስገባት ኩባንያውን በከፍተኛ ደረጃ እንዳዘመኑ ይነገርላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሚኒስትሯ በስራ ዘመናቸው የቴሌኮም ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ አስተማማኝ የዲጂታል መሰረት በመጣል እና የዲጂታል ፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ለሀገራዊ የዲጂታል ሽግግር ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።  ሚኒስትሯ በኢትዮ ቴሌኮም ከ 2010–2019ዓ·ም በነበራቸው ቆይታ በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ የአፍሪካ ምርጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በቾይሱል 100 አፍሪካ የነገ የአፍሪካ የኢኮኖሚ መሪዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ይታወቃል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories