የናይጄሪያ መንግሥት ዜጎቹ በአዲስ አበባ በኩል ሲጓዙ በከተማዋ ከፍተኛ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ምክንያት ሊከሰቱ ከሚችሉ የጤና እክሎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።
የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ከባሕር ጠለል በላይ 2,355 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ ዝቅተኛ የኦክስጅን መጠን ስላላት፣ ቀድሞ የልብና የመተንፈሻ አካላት ሕመም ባለባቸው መንገደኞች ላይ ከባድ የጤና ስጋት ልትፈጥር እንደምትችል ገልጿል።
እስካሁን ቢያንስ 16 ናይጄሪያውያን ከከተማዋ ከፍታ ጋር በተያያዙ የጤና ችግሮች ሕይወታቸው ማለፉንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መናኸሪያና ለናይጄሪያውያን ተጓዦች ዋነኛ መሸጋገሪያ (ትራንዚት) መሆኗ ይታወቃል። ጤነኛ ሰዎች የአየር ንብረቱን በቀላሉ ቢላመዱትም፣ ተጓዳኝ የጤና እክል ያለባቸው ዜጎች ግን ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የሕክምና ምክር እንዲያገኙ ተመክሯል።SECO


