የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት ሀሙስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ያካሄዳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ስብሰባ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ሀገሪቷን በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲመሩ መመረጣቸው የሚታወስ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ለመጀመሪያ ጊዜ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
በጉባኤውም የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ፡፡ ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡SECO


