በኢትዮጵያ የመማሪያ መጻሕፍትን በጥራትና በብዛት ለማምረት የሚያስችል ግዙፍ የማተሚያ ፋብሪካ በቻይናው “ቲደብሊው ሆልዲንግ ሊሚትድ” እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ትብብር ሊገነባ ነው።
ለፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ብቻ 30 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት የተመደበለት ሲሆን፣ በስምምነቱ መሠረት የቻይናው ኩባንያ 51 በመቶ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 49 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል።
ቲደብሊው ሆልዲንግ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን እና የሕትመት ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የፋብሪካውን ግንባታና የሥራ አመራር ይመራል ተብሏል።
ይህ ግዙፍ ፋብሪካ የተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍትንና የመምህራን መምሪያዎችን በአገር ውስጥ በማተም፣ ከውጭ የሚገቡ መጻሕፍትን ለመተካትና ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።SECO


