ኢትዮጵያ ለኤርትራ  የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነባት አስታወቀች

ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ  ታሪፍ ለኤርትራ  የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነባት ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ውሎአቸው ካነሱት ነጥቦች መካከል የኤርትራ ጉዳይ አንዱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ መንግስት የመንገድ ግንባታ ለመስራት እንዲሁም የኤሌክትሪክ ሀይል መሰመር በመዘርጋት በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ታሪፍ ክፍያ እንዲፈም ለቀረበለት ጥያቄ የእንቢታ መልስ እንደሰጠ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

በኤርትራ መንግስት  መዝገበ ቃላት ውስጥ ውስጥ ልማት የሚል ቃል  የለም ሲሉ ከሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ሁለት ነገሮችን እንደሚፈልግ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደኛው የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ጠላቶች ማስታጠቅ ማቆም እንዲሁም ሁለተኛው ለጋራ ልማት አብሮ መነሳት ነው ይህ ካልሆነ የኤርትራ መንግስት በማይታረም ስህተት ውስጥ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories