የአፍሪካ ህብረት እና የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት (ኦኢሲዲ) ባወጡት አዲስ የጋራ ሪፖርት፣ አፍሪካውያን አገራት ብድርን በአግባቡ ወደ ኢኮኖሚ ዕድገት በሚያመሩ ፕሮጀክቶች ላይ ካዋሉት የዕዳ ጫናቸውን መቀነስ እንደሚችሉ አስታወቁ።
በናይሮቢ ይፋ በተደረገው በዚህ ሪፖርት መሠረት፣ 23 አገራት ከፍተኛ የዕዳ ስጋት ውስጥ ቢገኙም፣ ብድር ለልማት ፋይናንስ ወሳኝ መሆኑ ይቀጥላል። በምርታማ ዘርፎች ላይ የሚደረግ የ93 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የኢኮኖሚ ዕድገትን በ1 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ወደ 557 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የወደፊት ብድርን እንደሚያድን እና ከ10 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተመላክቷል።
ይሁን እንጂ የብድሩ መጠን ብቻ ሳይሆን የፕሮጀክቶቹ ጥራት እና አፈጻጸም ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል። ባለፉት ዓመታት የተደረጉ ትላልቅ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ከፍተኛ የዕዳ ጫና መፍጠራቸው ይታወሳል።SECO


