ኢትዮ ቴሌኮም ዋናራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳስታወቁት ጥላ የፋይናንስ አገልግሎት በቴሌ ብር አማካኝነት ያለዋስትና ብድር፣ በረጅም ጊዜ የክፍያ አማራጭ የስማርት ስልክ ባለቤት መሆን ያስችላል።
በጥላ የዲጂታል ፋይናንስ ለብድር አገልግሎቶች አዋሽ ባንክ በዓመት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ለማቅረብ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መደረሱ ተነግሯል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በመቀናጀት ያስጀመረው ጥላየፋይናንስ አገልግሎት የዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ አካል እንደሆነ አስታውቀዋል።


