የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከታህሣሥ ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ መጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ ለሚካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 420 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ገለፀ።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በዚህ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የውጭ ምንዛሪ ጨረታው በየሁለት ሳምንቱ የሚካሄድ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ጨረታ 70 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን አስረድቷል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ ብሔራዊ ባንክ በቅርብ ቀናት ውስጥ ማለትም በህዳር 23 እና ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚያካሂደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ 100 ሚሊዮን ዶላር መመደቡም ተገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ግልጽና ተገማች አሠራርን ለማጠናከር ባለው ቁርጠኝነት መሠረት፣ በየሩብ ዓመቱ የሚደረጉ የጨረታ ግብይቶችን በየጊዜው የማሳወቅ ሥራ እንደሚቀጥል በመግለጫው ጠቅሷል።


