የምራቅ አፍሪካ የሕግ ማኅበረሰብ 30ኛ ዓመት የምስረታና ዓመታዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ – የምሥራቅ አፍሪካ የሕግ ማኅበረሰብ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና ዓመታዊ ኮንፈረንስ ከህዳር 17 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ የምሥራቅ አፍሪካ የሕግ ማኅበረሰብ ስምንት አገራትንና ከ46 ሺህ በላይ አባላትን ያቀፈ ሰፊ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጠበቆች ማኅበር በቅርቡ ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ ወደ ሥራ ቢገባም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአኅጉር ደረጃ ትላልቅ ጉባኤዎችን (ባለፈው ዓመት የተካሄደውን የአፍሪካ ጠበቆች ማኅበር ጉባኤን ጨምሮ) ማስተናገድ መቻሉ ጥንካሬውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በዚህ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት የሚመጡ የሕግ ማኅበረሰብ አባላት እንዲሁም በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ውስጥ ያሉ የሕግ ባለሙያዎች እንደሚታደሙ ይጠበቃል። የስብሰባው ዋና ዓላማዎች በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና የሕግ የበላይነት እንዲጎለብት፣ በአገራቱ መካከል ያለው ትስስር እንዲጠናከር እና በሕግ ዘርፉ ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲኖር ማስቻል መሆኑ ተገልጿል።

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories