ኢትስዊች (EthSwitch) እና ማስተርካርድ (Mastercard) በኢትዮጵያ ውስጥ ዓለም አቀፍ የክፍያ አቅሞችን ለማስፋት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ።
በመድረኩ ላይ የኢትስዊች ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ይለበስ አዲስ እንደገለፁት፣ ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው። ስምምነቱ የኢትዮጵያን የዲጂታል ክፍያ ሥነ-ምህዳር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የሀገሪቱን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው።
በተጨማሪም፣ ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን ለመቀበል እና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ዕድሎችንና ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።
የማስተርካርድ የምሥራቅ አፍሪካ ማናጀር የሆኑት ሼሪያር አሊ በበኩላቸው፣ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የክፍያ ምህዳር ጋር ያላትን ውህደት ለማፋጠን የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም በዓለም ዙሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዓለም አቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚዎችን ለማሳደግ ካለው የማስተርካርድ ዓላማ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።


