የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታጋይ ኑሩ እንደገለጹት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀይ ቡና ለቀማ ተጀምሯል።
አርሶ አደሩ ከለቀማ ጀምሮ እንዴት ማዘጋጀት እና ማጠራቀም እንዳለበት ግንዛቤ እንዲያገኝ ተደርጓል።
የዋጋ ትመና ስራዎች በባለስልጣኑ አማካኝነት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት ከዘርፉ እንደሚጠበቅ ጠቁመው 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የቡና ምርት ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው።


