ከተማ አስተዳደሩ ለባንኩ ያስረከበው 1ሺህ 287 የመኖሪያ ቤቶች ነው
የከተማው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት የከተማ አስተዳደሩ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ 380 ሺህ በላይ ቤቶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች አስተላልፏል።
ዛሬ የተመረቁት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቶቹ ለንግድ ባንክ ሰራተኞች ሲሆን በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ የተገነቡ ናቸው።
የተመረቁት ህንጻዎች ከ11 እስከ 18 ወለል ያላቸው 24 ሲሆኑ ሕንፃዎቹ ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን፣ የስፖርት ሜዳን፣ የመዝናኛ ስፍራዎችን ፣ የመኪና ማቆሚያ እና ሌሎች የጋራ መገልገያዎችን አካተው የያዙ ናቸው ።

