በጅቡቲ እየጣለ ባለው ዝናብ ምክንያት ትምህርት ቤች ሊዘጉ ችለዋል፡፡ በጣለው ዝናብ የተሸከርካሪ መንገዶችን በጎርፍ በመዘጋታቸው ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ የተጠቆመ ሲሆን አገልግሎት መስጫ ስፍራዎችም ሊዘጉ ችለዋል፡፡
የመንገዶች በጎርፍ መዘጋትና የተሸከርካሪዎች አለመንቀሳቀስ ተከትሎ በኢትዮጵያ ገቢ ወጪ ንግድ ላይ ጫና እንዳያሳድር ነው የተፈራው፡፡
የሀገሪቱ የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት በጎርፍ የተዘጉ መንገዶችን በመክፈት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡@seco


