በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት አለመኖር ለሥጋ ፋብሪካዎች ፈተና መሆኑ ተጠቆመ

በኢትዮጵያ የሚገኙ የሥጋ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንዳያመርቱ ካደናቀፏቸው ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት አለመኖር መሆኑን የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

ቋሚ ኮሚቴው በአዳሚ ቱሉና በሞጆ ከተማ የሚገኙ የሥጋ ፋብሪካዎችን የኦዲት ግኝት መሠረት በማድረግ ባከናወነው የመስክ ምልከታ፤ ፋብሪካዎቹ በቂ የግብዓት (የእንስሳት) አቅርቦት ባለማግኘታቸው ምክንያት ከአቅም በታች እያመረቱ መሆኑን አረጋግጧል። ይህም በዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን የውጭ ምንዛሬና አገራዊ ጥቅም እየቀነሰው መሆኑ ተመልክቷል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት እንደገለጹት፣ ለፋብሪካዎቹ በቂ የግብዓት አቅርቦት እንዲኖር ለአርሶ አደሮችና ለአርብቶ አደሮች አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል። በተጨማሪም የእንስሳቱን የጤና ሁኔታና የሕይወት ታሪክ በአግባቡ በመመዝገብ የውጭ ገበያ ተደራሽነትን ለማስፋት የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories