የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ድጋፍ ፖሊሲ ከሰብአዊ እርዳታ ወደ ንግድና ስልታዊ ጥቅም እያዘነበለ መሆኑ ተገለጸ

የአውሮፓ ሕብረት ለታዳጊ አገራት የሚሰጠውን የውጭ እርዳታና ድጋፍ ከመደበኛው ሰብአዊ ድጋፍ ይልቅ ለሕብረቱ ስልታዊ ጥቅምና ለቀጥታ ኢንቨስትመንት በሚውሉ ዘርፎች ላይ ለማተኮር አቅጣጫ መቀየሩ ተነገረ።

ሕብረቱ በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ ወሳኝ ማዕድናትን ለማግኘት፣ የኃይል አቅርቦትን ለማረጋገጥ እና መደበኛ ያልሆነ ስደትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን እያሰፋ ይገኛል።

ለዚህም እንደ ትልቅ ማሳያ የሚጠቀሰው ከዛምቢያ የኮፐር ቀበቶ እስከ አንጎላው ሎቢቶ ወደብ የሚዘረጋውና 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የሎቢቶ ኮሪደር (Lobito Corridor) የባቡር መስመር ፕሮጀክት ነው።

የአውሮፓ ሕብረት እና አባል አገራቱ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር በዚህ ፕሮጀክት ላይ 2 ቢሊዮን ዩሮ ኢንቨስት እያደረጉ ይገኛሉ።

የሕብረቱ የዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጆዜፍ ሲኬላ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደገለጹት፣ ይህ አዲስ የልማት ሞዴል አውሮፓ የምትፈልገውን የኮፐር (መዳብ) አቅርቦት እንድታገኝ የሚያደርግ ከመሆኑም ባለፈ ለአካባቢው የሥራ ዕድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር ይፈጥራል።

ሕብረቱ እ.ኤ.አ ከ2028 ጀምሮ ለውጭ ድጋፍ የሚመድበውን በጀት ከ108 ቢሊዮን ዩሮ ወደ 200 ቢሊዮን ዩሮ ለማሳደግ ማቀዱ ተመልክቷል።

ሆኖም ይህ በጀት እንደ ትምህርት ቤትና ሆስፒታል ካሉ መሠረታዊ የልማት ሥራዎች ይልቅ፣ ወደ ትልልቅ የኃይል፣ የማዕድን እና የዲጂታል መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መዞሩ አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን (NGOs) ስጋት ላይ ጥሏል።

ተቺዎች እንደሚሉት ይህ አካሄድ አውሮፓ ከቻይና እና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በምታደርገው የማዕድን ሽሚያ ውስጥ ለመሳተፍ ስትል የቆየችበትን የሰብአዊነት እሴት ለንግድ ጥቅም አሳልፋ እየሰጠች መሆኑን ያሳያል። የአውሮፓ ሕብረት በበኩሉ ይህ “ግሎባል ጌትዌይ” (Global Gateway) የተሰኘው ስትራቴጂ ታዳጊ አገራት በዕዳ ሳይዘፈቁ ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያግዝ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት መሆኑን ይሟገታል።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories