ባለሥልጣኑ ለገዳ ሴኩዩሪቲስ ዲለር አ.ማ. የአገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጠ

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለገዳ ሴኩዩሪቲስ ዲለር አ.ማ. (Gada Securities Dealer S.C.) የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ መስጠቱን አስታወቀ።

 ዛሬ ረቡዕ ታኅሣሥ 15 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተሰጠው ይህ ፈቃድ፣ ድርጅቱ በሀገሪቱ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አከናዋኝነት ዘርፍ እንዲሰማራ የሚያስችለው ነው።

ይህ አዲስ ፈቃድ የተሰጠው ኢትዮ ፊደልቲ ሴኩዩሪቲስ የመጀመሪያው የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አከናዋኝ ሆኖ ከተመዘገበ ከአራት ወራት በኋላ ሲሆን፣ ይህም በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትን ቁጥር ወደ ሁለት አሳድጎታል።

 ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባለሥልጣኑ የድርጅቱን የአራት ተሿሚ እንደራሴዎች ፈቃድ እና የስድስት የቦርድ አባላትን ሹመት ማጽደቁ ታውቋል።

ይህ ፈቃድ በአገሪቱ ውስጥ ፈቃድ ያገኙ ጠቅላላ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ቁጥር ወደ 14 ያደረሰ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪና ተደራሽ እንደሚያደርገው ተመልክቷል።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories