በትግራይ ክልል የሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ሂደት በዚሁ ሳምንት እንደሚጀመር ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል የሚከናወኑ የምክክር ሥራዎችን በያዝነው ሳምንት እንደሚጀምር አስታወቀ። የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በመጪው ጥር ወር መጨረሻ 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)  እንደገለጹት፤ በትግራይ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ተወካዮችን የማስመረጥ ተግባራት በዚሁ ሳምንት ይጀምራሉ።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ በሥራው የሚሳተፉ ሰዎችን የመመልመልና የማሰልጠን ሥራዎች ቀድመው እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል።

በትግራይ ክልል የሚከናወነው የምክክር ሂደት እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ መቀመጡን የገለጹት ኮሚሽነሩ፤ ይህም መላ ሀገሪቱን ያካተተ የምክክር መድረክ ለመፍጠር ለተያዘው ግብ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ የሥራ ጊዜ እስከ የካቲት አጋማሽ 2018 ዓ.ም ድረስ መሆኑን ያስታወቁት ፕ/ር መስፍን፤ ታሪካዊው ዋና ጉባዔ የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት በጥር ወር መጨረሻ እንደሚከናወን አረጋግጠዋል።

በዚሁ ጉባዔ ላይ ከመላ ሀገሪቱ የተወከሉ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚሳተፉም ተጠቁሟል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጀንዳዎችን የማሰባሰብና ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራዎችን ማጠናቀቁ ይታወሳል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነዉ።@seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

እስራኤል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አገሯ እንዳይገባ አገደች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አውሮፕላን በበረራ ሰራተኛው ምክንያት ወደ...

የፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ በሀገር ውስጥ፣ በአውሮፓ...

ግብፅ በጅቡቲ በወደብና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ያላትን ተሳትፎ ልታፋጥን ነው  

የካይሮ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን እንደማያስደስት ተነግሯል የግብፅ የልዑካን ቡድን በጅቡቲ ዋና...

Popular Categories