የኢትዮጵያ ብር በዓለም አቀፍ ደረጃ በዝቅተኛ የዋጋ ደረጃ ካላቸው ገንዘቦች ተርታ ተመደበ

የኢትዮጵያ ብር ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ያለውን ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በማጣቱ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአርጀንቲና እና ከቱርክ ቀጥሎ ሦስተኛው ደካማ መገበያያ ገንዘብ ሆኗል ተባለ።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ፣ የብር ዋጋ በተያዘው የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ ብቻ በ15 በመቶ ማሽቆልቆል አሳይቷል። ይህ የዋጋ መዳከም ብርን ከአርጀንቲናው ‘ፔሶ’ እና ከቱርኩ ‘ሊሬ’ በመቀጠል በዓለም የገንዘብ ገበያ ዝቅተኛ አፈጻጸም ካላቸው መገበያያ ገንዘቦች ተርታ እንዲሰለፍ አድርጎታል።

የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት፣ የብር ዋጋ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ኢትዮጵያ ካለባት የውጭ ዕዳ ሽግሽግ (Debt Restructuring) ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ነው። መንግሥት የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ብድር መልሶ ለማዋቀር ከአበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ መድረሱ የሚታወስ ቢሆንም፣ የሂደቱ መዘግየት በገንዘቡ ላይ ጫና ፈጥሯል።

ባለፉት ጥቂት ወራት የታየው የብር መዳከም በመደበኛውና በትይዩ (ጥቁር) ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት አባብሶታል። በአሁኑ ወቅት በመደበኛው ባንክ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 151 ብር አካባቢ ቢሆንም፣ በጥቁር ገበያ ግን እስከ 180 ብር ድረስ እየተመነዘረ ይገኛል።

ይህ የገንዘብ ዋጋ መዳከም በሸቀጦች ዋጋና በአጠቃላይ የኑሮ ውድነት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስተዋለ ይገኛል።@seco

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories