መጋዘኖችን በመፈተሽ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስጠንቅቋል
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከኢትዮጵያ ጥራጥሬ እና ቅባት እህሎች ላኪዎች ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው ባለፉት ወራት የጥራጥሬ እና የቅባት እህሎች ምርት የኤክስፖርት አፈፃፀም እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው የተነገረው ፡፡
እንደሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለጻ በሃገር ውስጥ ከፍተኛ የምርት ክምችት ቢኖርም ምርቱን ላኪዎች በክምችት ይዘውታል፡፡
በውይይቱ ላይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የኤክክፖርት የዋጋ ማሻሻያ መደረጉን ያስታወሰ ሲሆን ላኪዎች በክምችት የያዙትን ምርቶች በፍጥነት እንዲያወጡ እስስቧል፡፡
ላኪዎች ምርቶቹን በፍጥነት ካላወጡ ፍተሻ በማካሄድ መጋዘኖች እስከማሸግ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት በፀደቀው ደንብ መሰረት ምርቱን መልሶ በምርት ገበያ እስከመሸጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡@seco


