እስራኤል ለሶማሌላንድ እውቅና ሰጠች

እስራኤል ለሶማሌላንድ በይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ አገር ሆነች።

የሁለቱ አገራት መሪዎች በማህበራዎ ሚዲያ ገፃቸው ለሶማሌላንድ እውቅና መሰጠቱን አብስረዋል።

በዚህም መሰረት ሶማሌላንድ በአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምት በቀደመ የስልጣን ዘመን በተጠነሰሰው የአብርሃም ስምምነት አካል እንደሆነች የታወቀ ሲሆን መሪዋ አብዱራህማን መሀመድ በእስራኤል ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ግብዣ ቀርቦላቸዋል።

ሁለቱ አራት በመካከላቸው የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለመጀመር ኢንባሲ ይከፍታሉ ነው የተባለው።

ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የባህር በር ለኢትዮጵያ ለመስጠት በምትኩ ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠት ተስማምተው ነበር።

ሆኖም ሶማሌላንድን የግዛቷ አካል እንደሆነች የምታስበው ሱማልያ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማቷ ይታወሳል።

ሆኖም የሶማሌላንድ እውቅና እንድታገኝ በተለይ አንዳንድ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ፖለቲከኞች ግፊት እያደረጉ እንደሆነ ነው የሚገለፀው።

የአሁኑ የእስራኤል እውቅና መስጠት በተለይ ሌሎች አገራት መሰል መንገድ እንዲከተሉ የሚያደፋፍር ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።

ሶማሌላንድ ከቅኝ ግዛት በተናጠል ነፃ የወጣች ቢሆንም ከሱማልያ ጋር ነፃ በወጣች በቀናት ውስጥ እንድትተዳደር ሲደረግ ነበር።

ሆኖም ባለፈው 35 አመት በዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር እና ከቀረው ሶማሌ በተለየ በተረጋገጠ ሰላማዊ ሁኔታ ራሷን ማስተዳደር ችላለች።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories