ጨዋታው እየተቀየረ ነው

ፊተኞች ኋለኞች ወይስ ቀጣዩ የአለም ሁኔታ? እያስባለ ነው።

ቻይና የኦቶሞቲቭ እንደስትሪውን እንደ መርከብ ሁሉ በመሪነት ትረከብ ይሆን? ቀጣዩ ጨዋታ ምን ሊሆን ይችላል።

በቅርቡ እንደተሰማው እና ዜናውን ብዙዎች ማመን አቅቷቸው የኢንተርኔት መረብን በሰርች/ፍለጋ እንዲያጣብቡ ያደረገ ክስተት ከፈጠራ እና የረቀቀ ኢንደስተሪ ማእከሏ ከጀርመን ተሰምቷል።

ጨዋታው ወዲህ ነው።

በኦቶሞቲቭ ተባለ በኦቶሞቢል ደረጃ ማማ ላይ የሚቀመጠው ሜርሴዲስ ቤንዝ የቻይና ሞተር ሊጠቀም መሆኑ ነው የተነገረው።

የቻይናን እቃ ለሚጠየፉ የምእራቡ አለም ሰዎች መረጃው ከመዘግነን አልፎ ለማመን እጅግ ከብዷቸዋል።

ለዚህም ይመስላል ዜናው ከወጣ በኋላ ድጋሚ ለማረጋገጥ ሰርች ኤንጅናቸውን ያጨናነቁት።

ሜርሴዲስ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሱ ለታማኝ የምእራብ አገራት ደንበኞች ምን ፈጥሮባቸው ይሆን?

በርግጥ ቅንጡ መኪና አምራቹ እንደተናገረው ወደ ገበያ ለሚያስገባቸው የ3ኛ ትውልድ CLA ሞዴል የቤት መኪኖቹ የቻይና ሞተር የሚጠቀም ይሆናል።

አንዳንዶች ኩባንያው ልክ እንደ ሌሎች የጀርመን መኪና አምራቾች በቻይና ማምረቻ ስላለው ነው ብለው ያስቡ ይሆናል።

የዚህኛው ግን ይለያል።

ሜርሴዲስ ይፋ እንዳደረገው ለአዲሱ ሞዴል መኪና የሚጠቀመው ሞተር ከቻይናው ጄሊ የተሰኘ የመኪና አምራች የሚገዛ ነው።

ማስታወሻ: በቻይና መንገዶች በብዛት ከሚታዩ የቤት ኦቶሞቢሎች የጀርመን እና የአሜሪካ ብራንዶች ቀላል የሚባል ቁጥር የሌላቸው ብቻ አለመሆኑ ሳይሆን ተወዳጅነት ጭምር አላቸው።

የክላስ ጨዋታም እንዳለ ይታሰብ የሚሉም አሉ።

በርግጥ በቻይና በቀል የኤሌትሪክ መኪና ምርት ፈተና እየገጠማቸው እንደሆነ ነው እየተገለፀ የሚገኘው።

የቻይና በቀል የኤሌትሪክ መኪኖች ሽያጭ በአስደማሚ ደረጃ በአለም ላይ ከፍ እያለ መምጣቱ የዘርፉ ሜዳ ከተለመደው የምእራብ አለም እና ጃፓን መንገድ እየቀየረ ነው እያስባለ መሆኑ ይታወስ‼️

ነገሩ የፊቶቹ ለተናቁት ቦታ እየለቁ ይሆን እያስባለ ነው።

ቀጣዩ ዘመን ተወደደም ተጠላ የምስራቁ አለም ነው የሚሉቱ አሸናፊ እየሆኑም ይመስላል።@seco

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories