ከብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ ከውጭ ሀገር ገንዘብ በማስተላለፍ ኢትዮጵያ ከ41 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እንድታጣ አድርጓል የተባለው ተከሳሽ ፉአድ ተማም ላይ ክስ ተመሰረተ።
ተከሳሹ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ባንኮች በከፈታቸው የሂሳብ ቁጥሮች በመጠቀም፣ በውጭ ሀገራት ካሉ ግብረ-አበሮቹ ጋር በመመሳጠር ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ለተቀባዮች ማከፋፈሉ በዐቃቤ ሕግ ክስ ዝርዝር ተመልክቷል።
ይህ ገንዘብ በሕጋዊ የገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል ገብቶ ቢሆን ኖሮ ሀገሪቱ 41 ሚሊዮን 90 ሺህ ዶላር ታገኝ እንደነበር የገለጸው ክሱ፣ ተከሳሹ ያለ ፈቃድ የባንክ ሥራ በመስራት ወንጀል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ልዩ ወንጀል ችሎት ቀርቧል።@SECO


