ኢትዮ ቴሌኮም ለዕድለኛ ደንበኞች ሽልማት አስረከበ

ኩባንያው የስድስት ተጨማሪ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብርንም አካሄዷል

ኩባንያው  130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃ ግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሲያበረክት መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ እና የጅማ ባለዕድሎች፣ ሁለት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ (BYD) የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቁልፍ  አስረክቧል፡፡

ኩባንያችን በስልሳ አምስት ሳምንታት ውስጥ፣ 4 የኤሌክትሪክ መኪኖችን  እንዲሁም 13 ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለዕድለኛ ደንበኞቹ ቁልፍ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ከ127.8 ሚሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ ዋጋ ያላቸውን  ዘመናዊ ስማርት ስልኮች፣ ለንበኞች በየቀኑ እና በየሳምንቱ  የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ፣ እንዲሁም  የሞባይል ጥቅሎችን ሽልማቶች አበርክቷል።  በዛሬው ዕለትም የመጨረሻዎቹን ስድስት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዕጣ የማውጣት መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ በሚዘጋጅ ልዩ መርሃ ግብር ስድስቱን መኪኖች ለባለዕድሎች እንደሚያስረክብ ኩባንያው አስታውቋል፡፡@SECO      

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories