ዳሸን ባንክ  የተከፈለ ካፒታሉ 14.3 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ነው

ቅዳሜ ገበያ ከባንኩ ያገኘችው መረጀ እንደሚያሳየው ዳሽን ባንክ ከ30 ዓመት በፊት አሥራ አንድ ቅርንጫፎችን በአንድ ጀንበር ከፍቶ ሥራ ሊጀምር የቻለ ሲሆን ባንኩ የምስረታ በዓሉን እኤአ ከጃንዋሪ 1 ቀን 2026 ጀምሮ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት በተለያዩ ኹነቶች ማክበር ጀምሯል፡፡

የባንኩን የምስረታ በዓል አስመልክተው መልዕክት ያስተላተላለፉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ ዳሸን ባንክ ዘመንን የሚሻገር ራዕይ የነበራቸው አሥራ አንድ መስራቾቹ በኢትዮጵያ እንደ ራስ ዳሸን ተራራ በሩቁ የሚታይ ትልቅ የፋይናንስ ተቋም ለመመሥረት በነበራቸው ቀና ፍላጎትና ፅኑ ዓላማ የተነሳ የባንኩ ምስረታ እውን ሊሆን ችሏል፡፡

ከጃንዋሪ 1 ቀን 2026 ጀምሮ ለሚቀጥሉት ተከታታይ ሦስት ወራት፤ ዳሸን ባንክ የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን የነበረውን ፋና ወጊ ሚና፣ ለደንበኞቹ የገባውን ቃልኪዳን በመጠበቅ እንዲሁም በሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ ባንኩ ያለፈባቸውን ሂደቶች በማስታወስና በሁሉም መስክ ደማቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የቀደሙ ባለውለታዎቹን በሚዘከሩ የተለያዩ ኹነቶች ያከብራል ብለዋል፡፡

በ11 ባለአክሲዮኖች የተቋቋመው ዳሸን ባንክ በአሁኑ ወቅት  የባለአክሲዮኖቹ ቁጥር 4,974 ሲደርስ በአስራ አንድ ቅርንጫፎች የተጀመረው የባንኩ አገልግሎት ደግሞ ወደ 906 ቅርንጫፎች ደርሷል፡፡ የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም ከ14.9 ሚሊዮን ብር ወደ 14.3 ቢሊዮን ብር መድረሱንነው ተገለጸው፡፡

የዳሸን ባንክ የተጠናቀቀው የበጀት ዓመት (2017) የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ከ254 ቢሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ደግሞ 202.2 ቢሊዮን ብር ሆኗል፡፡ በተጨማሪም የዳሸን ባንክ የደንበኞቹ ቁጥር ከስምንት ሚሊዮን በላይ ደርሷል፡፡@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories