ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2014 ዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ያወጣችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ዋጋ፣ በለንደን የአክሲዮን ገበያ ላይ በአሜሪካ ዶላር የ3 ሳንቲም ጭማሪ ማሳየቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። ይህ የዋጋ ጭማሪ የተመዘገበው የኢትዮጵያ መንግሥት ዩሮቦንዱን ለማሸጋሸግ ከቦንዱ ያዥ ኢንቨስተሮች ኮሚቴ ጋር ባለፈው ሳምንት በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ነው።
የዩሮቦንዱ ዋጋ መጨመር ኢንቨስተሮች ለቦንዱ ያላቸው ፍላጎት ማደጉን የሚያመለክት ሲሆን፣ በአንጻሩ ኢትዮጵያ ለቦንዱ የምትከፍለው የወለድ መጠን መቀነሱን ያሳያል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዩሮቦንዱን 45 በመቶ የያዙ ኢንቨስተሮችን ከወከለው ኮሚቴ ጋር ስምምነት የደረሰው፣ ቦንድ ያዦቹ በዩሮቦንዱ ዋጋ ላይ የ15 በመቶ ቅናሽ (Haircut) እንዲያደርጉ መንግሥት ባቀረበው ሃሳብ መሠረት መሆኑ በዘገባው ተመልክቷል።
በሌላ በኩል፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይህ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በቦንድ ያዦች መካከል የተደረሰው ስምምነት፣ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ከፈቀደው የ3.6 ቢሊዮን ዶላር የብድር ፕሮግራም ዓላማ ጋር የሚጣጣም መሆን አለመሆኑን በቀጣይ ቀናት እንደሚገመግም ሮይተርስ ዘግቧል።@SECO


