የጀርመን ወግ አጥባቂው የክርስቲያን ሶሻል ዩኒየን (CSU) ፓርቲ፣ የአውሮፓን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማሳለጥና የአውሮፓ ኩባንያዎችን ዝርዝር ለማበረታታት ታስቦ የቀረበውን የአውሮፓ የጋራ የአክሲዮን ገበያ የመመስረት ጥሪ እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ሲ.ኤስ.ዩ የአውሮፓ የካፒታል ገበያን ማጠናከር ስኬታማ የጀርመን ኩባንያዎች በሀገር ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ያምናል።
ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ ግልጽ የሆነ የመሪነት ሚና ለመጫወት ማቀዱን የገለጸ ሲሆን፣ የአውሮፓ የጋራ የአክሲዮን ገበያ ዋና መሥሪያ ቤት በአውሮፓ ህብረት ትልቁ ኢኮኖሚ በሆነችው ጀርመን ውስጥ እንዲቀመጥ ጥረት እንደሚያደርግም አስታውቋል።
ይህ ዕቅድ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻንስለር ፍሪድሪች ሜርዝ ባለፈው ጥቅምት ወር የቀረበ ሲሆን፣ አውሮፓን ለንግድና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ስፍራ ለማድረግ ያለመ ነው። ሃሳቡ በአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዝዳንት ክሪስቲን ላጋርድ፣ በጀርመን ፋይናንስ ሚኒስትር ላርስ ክሊንግቤይል እና በቡንደስባንክ ፕሬዝዳንት ዮአኪም ናገል ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘቱ ተገልጿል።@SECO


