በቬንዙዌላ የተከሰተውን ድንገተኛ የፖለቲካ ለውጥ ተከትሎ፣ የቻይና የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት የዘይት ምንጫቸውን ወደ ኢራን እና ሩሲያ እያዞሩ መሆኑ ተሰምቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ከአዲሱ የቬንዙዌላ አስተዳደር ጋር የነዳጅ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ፣ ቀደም ሲል ወደ ቻይና ይላክ የነበረው ዘይት መቋረጥ መጀመሩ ለዚህ ለውጥ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
የቻይና የግል የነዳጅ ማጣሪያዎች የቬንዙዌላውን ድፍድፍ ዘይት ለመተካት የኢራንን ምርት በስፋት ማዘዝ የጀመሩ ሲሆን፣ የኢራን ዘይት በዓለም ገበያ ካለው ዋጋ በበርሜል የ10 ዶላር ቅናሽ ያለው መሆኑ ለቻይናውያን ገዢዎች ትልቅ ማበረታቻ ሆኖላቸዋል።
ቻይና በአሁኑ ወቅት የ75 ቀናት የነዳጅ ክምችት ቢኖራትም፣ አዲስ ጭነት በፍጥነት ካልደረሰ ግን እስከ መጋቢት ወር ድረስ የአቅርቦት እጥረት ሊያጋጥማት እንደሚችል ተመልክቷል። ይህ የቬንዙዌላ የፖለቲካ መቀየር ቻይና ከኢራን እና ከሩሲያ ጋር ያላትን የነዳጅ ትብብር ይበልጥ እንድታጠናክር እያስገደዳት ይገኛል።@SECO


